Best products and memorable times

የሳሙና ማምረቻ ማሽን ሙሉ ለሙሉ ሳሙናን አምርቶ ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል
ይህ የሳሙና ማምረቻ ማሽን ሙሉ ለሙሉ ሳሙናን አምርቶ ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችሉ ክፍሎችን ከመቀላቀያ / Sigma Mixer እሰከ መዳመጫ ፤ ከቅርፅ ማውጫ እስከ አርማ ማተሚያ ያሉ ክፍሎችን በማሟላት በአንድ ሰዓት ብቻ መቶ ኪሎ ግራም ሳሙና ለማምረት የሚያስችል ማሽን ነው።
ማሽኑ ለአጠቃቀም ቀላልና በቶሎ ሊለምዱት የሚያስችል ሲሆን ስሪ ፌዝ የኤሌክትሪክ መስመር የተዘረጋለትና ከማስረከባችን በፊት ደንበኛቻችን ባሉበት የምርት ሙከራ ፤ ነፃ የአጠቃቀም ስልጠናን ከመስጠት በተጨማሪ ለማምረቻ የሚሆኑ ግብአቶችን ከሚያቀርቡ ድርጅቶች ጋር እናገናኝተን የአንድ አመት የጥገና ዋስትና ከመለዋወጫ አቅርቦት ጋር እንሰጣለን ። /This soap making machine is a machine providing all the necessary parts needed to produce and market soap, from the Sigma mixer to the miller, from the mold maker to the logo stamper & that can produce 100 kilograms of soap in just one hour. The machine is easy to use and can be quickly adapted to, and the Three phase electric line is installed .
Before delivery, we taste the machine in the presence of the customers. In addition we provide free usage training, we also provide one year maintenance warranty with spare parts supply and connect with companies that provide production inputs.

ጥራት የሚጀምረው ከጋራ መግባባት ነው
ጥራት የሚጀምረው ከጋራ መግባባት በመሆኑ ከንድፍ ሐሳብ እስከ ጥሬ እቃ ማዘጋጀት ከመቁረጥ እስከ ማስተካከልና ኤሌክትሪክ ገጠማ፤ እያንዳንዱን የብረት ክፍል በደቂቅ ልኬት በማገናኘት ማሽኑ ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት የምህንድስና ስታንዳርዱን ማሟላቱን የምናረጋግጥበት ዝርዝር የሥራ እንቅስቃሴ / A deep look into our meticulous process starting with team brainstorming and design, followed by precision cutting, welding, and fixing, all leading to a final technical audit to ensure the physical machine exceeds its theoretical design before reaching the client.

የምንጣፍ መጭመቂያ ማሽን / carpet spinner machine
በብዙ መልክ አዲስ ተሻሽሎ የቀረበው የምንጣፍ መጭመቂያና ማድረቂያ ማሽን ከ4 - 5 ደቂቃ ባለ ጊዜ ውስጥ ከ94-96% የሚሆነውን ውሃ የሚያደርቅ በሰዓት ከ8 እስከ 12 ምንጣፎችን በማድረቅ ትርፋማ እንዲሆኑ ያደርጎታል። ከፍተኛ ጥራት ካለው እስቴንለስ እስቲል መሰራቱ እድሜውንያራዝማል የአገልግሎት ጫናዎችን በመቋቋም እንዲያገለግሎት ያስችሎታል። በአገልግሎት ጊዜ የሚፈጥረውን ቫይብሬሽኑን መቋቋም የሚያስችለው "shock absorber suspension system" ተገጥሞለታል።አውቶማቲክ መቆጣጠሪያ መሰረት በራሱ መጭመቁን የሚያቆምበትና ለአያያዝና ለማጓጓዝ ምቹ እንዲሆን በማድረግ ጠቅልሎ የሚያዘጋጅ ሲስተም ተዘርግቶለታል።ማሽኑን በተለያየ አይነት የመጠንና ኤሌክትሪክ ሃይል
የሞዴል አማራጮች ዲዛይን አድርገን አቅርበናል።ከነዚህም በተጨማሪ የአጠቃቀም ስልጠናን ፣ የአንድ አመት የጥገና ዋስትና ከመለዋወጫ አቅርቦት ጋር እንሰጣለን ። /This newly improved, high quality carpet spinner and dryer, drying 94–96% of water in 4–5 minutes and processing 8–12 carpets per hour. It's built with stainless steel and includes a shock absorber suspension to handle heavy use and vibration. Has featuring of automatic stop and a system that rolls up the carpet. The machine is available in various sizes and power options, and purchases include usage training, a one year warranty, and spare parts

milk pasteurizer machine
ይህ ማሽን በአንድ ጊዜ 50 ሊትር ወተትን ፖስቸራይዝ ማድረግ የሚያስችል ማሽን ሲሆን ወተቱን በተፈለገው መጠን ካሞቀና ካፈላው በኋላ በሚፈለገው መጠን በማቀዝቀዝ ደህንነቱ የተጠበቀ ወተት ያዘጋጃል።
የተሰራውም ሙሉ በሙሉ ከእስቴንለስእስቲል ሲሆን ባለ ደብል ጃኬት ማሞቂያ ስርዓት ያለውና ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ ዲጂታል የሙቀት መቆጣጠሪያ ተገጥሞለት በስንግል ፌዝ መስራት መቻሉ ደሞ በቤቶም ሆነው ለመስራት ያስችሎታል። ከዚህም በተጨማሪ ከ50 ሊትር ጀምሮ የተለያየ የመጠን አማራጮችን በትእዛንዝ እንቀበላለን ፤ ማሽኑንም ሲወስዱ ነፃ የአጠቃቀም ስልጠና ከአንድ አመት የጥገና ዋስትናና ከመለዋወጫ አቅርቦት ጋር እንሰጦታለን።/This machine can pasteurize 50 liters of milk at once. It heats and boils, then cools down to the desired level, producing safe milk.
It is entirely made of stainless steel, has a double jacket heating system, and has a digital temperature controller that is easy to use.
It operate in a single phase, so it can be used at home. Furthermore, We take orders for a range of sizes, beginning with 50 liters and offer a one year warranty and a supply of spare parts, as well as we provide free training on how to use the machine.

በህብረት ማሽኖችን የማምረታችን ሂደት
እያንዳንዱ የምናመርታቸው ማሽኖች በውስጡ የባለሙያዎቻችንን ጠንካራ የስራ ባህልንና ተዋህዶ በህብረት ማሽኖችን የማምረታችን ሂደት እለት እለት በትጋት የመስራታችን የመረዳዳትና የመደጋገፋችን ውጤት ናቸው።/ Every machine we manufacture is the outcome of our professionals' strong work ethic and the cooperative process of producing machines together, working hard each day, and supporting and assisting one another.

ጥሬ እቃዎች ወደ ወርክሾፖችን
ከጥሬ እቃነት ወደ ማሽንነት ከመለወጣቸውና ከብረት እጥፋትና ከብየዳ በፊት የማሽኖቻችን ክፍሎች እንዲሆኑ የታቀደላቸውን ጥሬ እቃዎች ወደ ወርክሾፖችን እናጓጉዛለን ይህንንም ስናደርግ ከጋራ የስራ ትጋታችን ጥራት ወዳለው አምራች ሃይል ለማሻገር በመስራት ነው።/From steel/ raw material to machine and from effort to energy, Before the sparks fly and the welding begins, We unload the future with strength and heart

Cosmetic & Detergents making machine
ይህ ማሽን ሙሉ በሙሉ ከእስቴንለስ እስቲል የተሰራ እና "ደብል ጃኬት ማሞቂያ " የአመራረት ስርዓት የተሰራ ሲሆን በሞቃትም ሆነ በቀዝቃዛ ምርት አመራረት ሂደት ውስጥ የሚሰሩትን ክሬም ፣ ሎሽን ፣ ሻምፖዎች ፣ ኮንዲሽነሮች ፣ ፈሳሽ ሳሙናዎችንና ሌሎች ተያያዥ ምርቶችን ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ማምረት እንደሚችሉ ያረጋግጥሎታል።ማሽኑን ከማስረከባችን በፊት የሙከራና የስልጠና አገልግሎት ከአንድ አመት የጥገና ዋስትናን እንሰጣለን።/One powerful machine, built with 100% 304 food grade stainless steel and double jacket heating, preform either in hot or cold process and delivers creams, lotions, shampoos, conditioners and detergents with precision, durability and guaranteed reliability

ጳጉሜ ፬
ጳጉሜ ፭
አዲሱን ዓመት ለመቀበል የሰዓታት እድሜ ቀርተውናል የቀረውንም ጊዜ በመታደስና አብሮነትን እንቁጠር።
ዛሬ ላይ አንቆምም ፤ ዛሬ ላይ ሰርተን ለነገ እናቅዳለን ! በህብረት ወደፊት!
በ2017 ዓ.ም የጳጉሜን የመጨረሻ ቀን ከስራችን ያለማቋረጥ ወደ ፊት እንጓዛለን።
ተባብረን በዛሬው ጥረታችን የነገው ተስፋችንን
በጋራ እንቀርፃለን።
እንኳን አደረሳችሁ
Pagume 5
We don’t stop today together we shape tomorrow!
This is the final day of Pagume, and we keep moving forward without pause.
United in effort, united in hope, we shape tomorrow together.
The New Year is just hours away, and it’s time to celebrate renewal and togetherness.
Happy new year

ጳጉሜ ፬
ጳጉሜ ፬
ትላንትን በስራ ፤ ዛሬን በትጋት ፤ ነገን በተስፋ!
ጠንክረን መሥራታችን ዓመቱን አሳልፎልናል ፣ የየለት ትጋታችን ደሞ ዛሬ ላይ ሲያመጣን ተስፋችን ደሞ ለነገ መንገድ ያበራል። መጪው አዲሱን ዓመትም ሁለት ቀን ብቻ ሲቀረው በደስታ መንፈስ እንቀበለዋለን።
እንኳን አደረሳችሁ
Pagume 4
Yesterday with work, today with effort, tomorrow with hope!
Hard work has carried us through the year, effort drives us today, and hope lights the way for tomorrow. With just a little time left, we welcome the New Year with open hearts and joyful spirit.
Happy new year

ጳጉሜ ፫
ጳጉሜ ፫
ትላንት ላይ ሆነን ለዛሬ፣ ዛሬ ላይ ሆነን ለነገ
እንሰራለን!
ይህም የእያንዳንዱ ቀን ትናንት ትምህርት ሰጥቶን ሲያልፍ ፤ ለዛሬ ብርታት ሲሰጠን ለነገ ደግሞ ደስታን ይሆነናል። የአዲስ አመት መምጫው ቀን ቆጠራው ሲቀጥል ሊመጣ ያለውን አዲስ ዓመት በተስፋ እንጠባበቃለን።
ትላንት የተሰራ ዛሬ ፤ ነገን ይገነባል!
እንኳን አደረሳችሁ
Pagum 3
Yesterday built today, today builds tomorrow!
Each day has its purpose yesterday gave us lessons, today gives us strength, and tomorrow will give us joy.
As the countdown continues, we look forward with hope to the New Year that is almost here.
Yesterday made today; It builds tomorrow.
Happy new year

ጳጉሜ ፪
ጳጉሜ ፪
ዛሬ ላይ ሆነን ለነገ እንሰራለን!
ጳጉሜ ዛሬ ስራችን ላይ ያለን ትጋትና ጥረት የነገን ስኬታችንን እንደሚቀርጽ ያስታውሰናል።
እያንዳንዱ ተግባር ፣ ህልምና ተስፋችን ለመጪው ብርሃን እየቀረበ ለሚመጣው አዲስ አመት ያዘጋጀናል።
እንኳን አደረሳችሁ
Pagume 2
Rooted in today, working for tomorrow!
Pagume reminds us that the effort we give today shapes the success of tomorrow. With every action, every dream, and every hope, we prepare for the New Year that is coming closer with light and celebration.
Happy new year

ጳጉሜ ፩
ጳጉሜ ፩
ዛሬ ላይ ጠንክረን በመቆም ነገን እናያለን!
ስለዚህ ወደ ጳጉሜ ስንገባ በተስፋ እና በደስታ ፀንተን ፤
ዛሬ ጥንካሬን, ነገ ደሞ አዲስ ጅማሮችን እንደሚሰጠን አምነን ነው።
አዲሱ ዓመት በቅርብ አድማስ ላይ ነውና የሚመጣበትን ቀኑን አብረን በደስታ እንቁጠር።
እንኳን አደረሳችሁ!
Pagume 1
Standing strong today, we’ll see tomorrow!
As we step into Pagume, we stand firm with hope and excitement.Today gives us strength, and tomorrow promises new beginnings. The New Year is on the horizon, and together we count the days with joy.
Happy new year

milk incubator/ የወተት ማርግያ ማሽን
በብዛት አምርተን ያቀረብናቸው የወተት ማርጊያ ማሽኖቻችን 50 ሊትር ወተት በአንድ ጊዜ የማርጋት አቅም ያለው ሲሆን በተለያየ መጠን እንዲሰራ ምቹ ተጀርጎ ዲዛይን የተደረገ በመሆኑ በደንበኛች ፍላጎት መሰረት የመያዝ አቅማቸውን በመጨመር ፍላጎቶን እናሟላለን።የወተት ተዋፅኦ ላይ ፤ በግል ወይም በጋራ ለሚሰሩ ገበሬዎች ፣ የወተት ምርት በማቀነባበር ለንግድ ስራቸው ለሚያዘጋጁ እርጎ አቅራቢ ድርጅቶችና ማሽኑን በብዛዛት ወስደው ለሚያከፋፍሉ ልዬ ምርጫ ነው

Manuel churner machine / በእጅ የሚሰራ ወተት መናጫ ማሽን
በፍኖት ኢንጂነሪንግ ስራዎች ባህላዊውን የወተት መናጥ ሂደት አስተማማኝ ከሆነው የፈጠራ ስራን ጋር በማዋሀድ በእጅ የሚሰራ የወተት መናጫ ይዘንላችሁ መጥተናል። ማሽኑ ለታታሪ ገበሬዎችና የወተት ተዋጽኦ አምራቾች የተሰራ ሲሆን ። የኤሌትሪክ ሃይልን የማይጠቀም መሆኑ ደሞ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ላለባቸውና የኤሌክትሪክ መስመር ላልተዘረጋባቸው ቦታዎች ተመራጭ ያደርገዋል።
ማሽኑ ከፍተኛ ጥራት ካለው የማይዝ ብረት የተሰራ መሆኑ የወተቱን ንፅህና ለመጠበቅ፣ የሚያመርቱት ምርት ላይ እምነት ለማሳደር ፣ ማሽኑ ረጅም እድሜ እንዲኖረው ለማስቻልና ለፅዳት ቀላል እንዲሆን ያስችላል። በኛው የተመረተ በመሆኑ የመለዋወጫ አቅርቦት እንዲያገኙ በማድረግ የአንድ አመት የጥገና ዋስትና እንሰጣለን/At Finot Engineering, we designed for hardworking farmers and dairy producers by blend tradition and innovation, with our manual milk churning machine. It is fully hand operated and works perfectly without electricity. Made from high quality stainless steel for hygiene, durability, easy to clean, reliable, and locally manufactured with spare parts and 1year warranty.

Automatic cup sealing machine / ማሸግያ ማሽን
ይህ አውቶማቲክ ማሸጊያ ማሽን በአንድ ጊዜ 4 ኩባያዎችን በፍጥነትና በጥራት የማሸግ አቅም ያለው ሲሆን። ጁስ፣ እርጎ፣ የለውዝ ቅቤ፣ ማር፣ ካችአፕ፣ ሌሎች ተያያዥ ምግቦችንና እንዲሁም ምግብ ነክ ያልሆኑ ፈሳሾችን እና ጠጣር ነገሮችን በማሸግ ምርቶቻችሁን ጥራታቸውን እንደጠበቁ ለማቆየትና እንዳይፈስ በመከላከል ያስችላል። ማሸጊያ ማሽኑ ለምግብ ቤቶች፣ ለጭማቂ ቤቶች እና ለአነስተኛ ፋብሪካዎችና ለምግብ ሥራ ፈጣሪዎች ተስማሚ ነው። እንዲሁም የደንበኛን የማሸጊያ ፍላጎቶች ለማሟላት ለማንኛውም የእቃ የይዘት መጠንና ቅርፅ ትዕዛዞችን እንቀበላለን።/This automatic sealing machine seal 4 cups at once with speed and precision and it is perfect for juice, yogurt, Peanut butter, honey, ketchup, other related takeaway foods and also handles some none food related liquids and solids, keeping your products fresh and leak-proof. Ideal for restaurants, juice bars, and small factories. We also accept custom orders for any cup size, shape, or sealing style to fit your packaging needs

Team work / በጋራ መስራት
ማሽኖች እራሳቸውን አይገነቡም! ቁርጠኝነት፣ ችሎታ እንዲሁም እንደኛ ያለ በቡድን የሚሰራና በወርክ ሾፕ ከመጀመሪያ ዲዛይን እስከ መጨረሻው አቅርቦት ድረስ የሚሰራ ሰራተኛን የፈልጋል እንጂ። ይህንንም ምክንያት በማድለግ ፍኖት ኢንጂነሪንግ ስራዎች በሙሉ ኃይል፣ አንድ ቡድን በመሆን ፤ አንድ ዓላማ ይዞ ፤ ደረጃውን በጠበቀ ሁነታና በላቀ ብቃት ይሰራል/Machines don’t build themselves, it takes determination, skill, and also a workshop with a teamwork like this, where first design to the final delivery. For this reason Finot engineering works in full force, one team, one purpose, in well standard and excellence

የወተት ማርጊያ ማሽን/Milk incubator machine
ይህ በተለያየ የመጠን አማራጭ የቀረበ የወተት ማርጊያ ማሽን አይነት ሲሆን ፤ ይሄኞው 50 ሊትር በአንድ ጊዜ የማርጋት አቅም ያለው ነው። የሙቀት መቆጣጠሪያ ስርዓቱ እና ሃይል ቆጣቢ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል /Our Milk incubator machine is available in different size options; this one has a capacity of 50 liters at a time. Its temperature control system and energy efficiency makes it unique.

ደንበኞቻችንን/our customer
በፍኖት ኢንጂነሪንግ ስራዎች የእያንዳንዱ አዲስ እና ቋሚ ደንበኞቻችንን ጉብኝት አስፈላጊ ነው ፤ ስራችንን የተመለከቱ ብቻ ሳይሆን ምርታማ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን ማሽነሪ ላይ ኢንቨስት ያደረጉትንም ደንበኞችን በማስተናገዳችን ደስታ ይሰማናል።/ At finot engineering works, every visit matters ,we are honored to host clients who not only witnessed our work but invested in our machinery solutions.



















































































































































